Asset Publisher Asset Publisher

Back

ሁለተኛው ዓመታዊው አገር አቀፍ የባዮቴክኖሎጅ የምርምር ግምገማ ፎረም /National Research Review Workshop / በኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት መካሄድ ጀመረ ፡፡

ከግንቦት 9-10/2011 ዓ.ም. የሚቆየው ይህ አውደ ጥናት ዋና ዓላማው በዘርፉ እተካሄዱ ያሉትን የተጠናቀቁ፤ በሂደት ላያ ያሉና አዳዲስ ፕሮጅክቶችን ለመለየት፤ የምርመር ድግግሞሽን ለመቀነስና ለአዳዲስና በሂደት ላይ ላሉ ፕሮጅክቶች የተቀላጠፈ የሀብት አጠቃቀምና አሰራር እንዲኖር ለማድረግና ወደፊት የአገሪቱን ችግር ለመፍታት በሚያስችል መልኩ ትላልቅ ፕሮጅክቶችን በጋራ ለመስራት እንዲቻል ተደርጎ የተዘጋጄ እንደሆነ ተገጧል፡፡
የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ካሳሁን ተስፋዬ ስብሰባውን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር የአየር ንብረት ለውጥ፤ የአካባቢ መራቆትና ምግብ ዋስትና ችግሮች ለዓለማችን የተጋረጡባት ሥጋት መሆናቸውን አውስተው በፍጥነት እየጨመረ ለመጣው የሕዝብ ቁጥር ምንም በአካባቢ ላይ ጉዳት ሳያመጣ የምግብ፤ የውሀ፤ የመጠለያና ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ማቅረብ መቻል ዓለም የተቀበለው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ ረገድ በባዮሳይንስ ምርምርና ኢኖቬሽን ድንበር ተሸጋሪ ከሆኑ አካላት ጋር የአካባቢና ዓለም አቀፋዊ ትብብር እንዲኖር ማድረግ ዓለማችን የተጋረጡባትን ችግሮች በጋራ ለመቀረፍ አስፈለጊ ነው ብለዋል፡፡
በአገራችንም የዘላቂ ልማት ግቦችንና የትራንስፎርሜሽንን አጀንዳን ለማሳካት የሚቀረጹ እሰትራቴጅዎች የምርምርና ኢኖቬሽን ሐሳቦችን በዋናነት ማካተት ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡
በባዮሳይንስ የሚደረጉ የጥናት፤የልማትና የኢኖቬሽን ሥራዎች ለአንድ አገር ልማትና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት እንዲሁም ለሥነ-ምህዳር አያያዝ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ ዘመናዊ ባዮቴክኖሎጅ በግብርናም ይሁን በሌሎች ዘርፎች ለተጋረጡብን አያሌ ተግዳሮቶች ኹነኛ መፍተሄ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑ ተወስቷል፡፡ ባዮቴክኖሎጅ ለመጪው ጊዜ ሕይወታዊ ኢኮኖሚ የሚገነባ መሆኑ ብዙ ማረጋገጫዎች አሉ፡፡
ኢትዮጵያ ባላት ሰፊ የብዝሃ ህይወት ተላያይነት ባዮቴክኖሎጅን መጠቀም መቻሏ በዓለም አቀፍ ገበያ የተወዳዳሪነት አቅም (advantage) የሚሰጣት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡
ይሁን እንጂ ባዮቴክኖሎጅ እንደዲያድግና ለአገራችን የኢኮኖሚ እድገት በጎ አስተዋጽዎ እንዲኖረው ለማድረግ በጣም የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራትና አስፈላጊ ምርመርና የልማት መሰረተ ልማቶችን ማሟላት እንደሚያስፈልግ ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡
አክለውም ምንም እንኳ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የስልጠናና የምርመር ፕሮግራሞችን እያካሄዱ ቢሆንም አሁን ባለበት ደረጃ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽዎ ለማድረግ በጥሩ መሰረት ላይ ነው ለማለት እንደማያስችል ተናግረዋል፡፡
አገራችን በባዮቴክ መሰረተ ልማት ላይ እየተደረገ ባለው ከፍተኛ ኢንቨስተማንት የበለጠ ተጠቃሚ መሆን እንድትችል የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የዋና ላብራቶሪና በእየካባቢው በስድት ክላስተሮች የሚቋቋሙ በማዕከላዊ ፤ በሰሜን፤ ሰሜን ምዕራብ፤ በደቡብ፤በምራብና ምስራቅ ኢትዮጵያ ፕሮጅክቶችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
ደ/ር ካሳሁን ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመው በዘርፉ ምርምር የሚያደርጉ ተቋማትን በማቀራረብና የምርምር መሰረተ ልማትን በጋራ በመጠቀም የተፈለገው ውጤት ለማምጣት እንድንችል ነው ብለዋል፡፡ ለአብነትም አገር አቀፍ ኤችፒቪ ኮንሶርቲየም /Natioal HPV consortium/ እንዲቋቋም ኢንስቲትዩቱ የማመቻቸት ሥራ እንዳከናወነ አስረድተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ የአካባቢያዊ የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን ገልጸው ይህም የሚሆነው ምርምር ተቋማትንና ዩኒቨርስቲዎችን እንደ ተቋሙ አጋር በመቁጠርና በእነርሱም ላይ በመተማመን እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
………………………………………………………………………………........
የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኃይሉ ዳዲ በበኩላቸው ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ ኢንስትቲትዩቱ በየየአያመቱ የሚያካሂደው አውደ ጥናት በዘርፉ የሚሰሩ ምርምሮች ገምግሞ ጠንካራ ጎኖችን በማስፋት ክፍተተቶችን በወቅቱ ለማረም፤ መንግስትም በመደበው በጀት ምን ያህል ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ለማወቅ እንደሚያስችለው የመድረኩን ጠቀሜታ ተናግረዋል ፡፡ በሌላ በኩልም ነባር ተመራማሪዎች ለወጣት ተመራማሪዎች ልምድ በማካፈል ረገድ ሰፊ ጠቀሜታ እንዳለውም ገልጠዋል ፡፡ በመጨረሻም በዓመት አንድ ጊዜ በአንድ ላይ ተገናኝተው መወያየት መቻል ለዘርፉ ምሁራን ጥንከሬ እንደሚፈጥርላቸው አስረድተዋል፡፡
ተሳታፊዎች በሦስት ክፍሎች /thematic areas/ ግብርና ባዮቴክሎጂ፤ ጤናባዮቴክኖሎጂ፤ በኢንዱስትሪና አካባቢ ባዮቴክኖሎጅ ተከፋፍለው በሚቀርቡ የጥናት ወረቀቶች ላይ ውይይታቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡
በአውደ ጥናቱ ላይ 120 የሚያህሉ ተሳታፊዎች በአገሪቱ ከሚገኙ 40 የሚያህሉ ምርምር ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ተማራማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
………………………………………………………………………………………
ባለፈው ዓመት በተካሄደው በመጀመሪያው አገር አቀፍ ምርምር አውደ ጥናት 210 የሚያህሉ የምርምር ፕሮጀክቶች ለውይይት መቅረባቸው ይታወሳል፡፡