Asset Publisher Asset Publisher

Back

የኢትዮያ ባዮቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ለለሎች እድሜ ጠገብ ተቋማት እንደ ሮል ሞደል መወሰድ እንደሚችል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሐብትና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ገለጹ፡፡

ይህንን የተናገሩት 40 አባላትን ያያዙ የሰው ሐብትና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጅ እንስቲትትን ዛሬ መጋቢት 11/2011 በጎበኙበት ወቅት ነበር ፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ዘርፎች እያካሄደ ያለውን ምርምሮች የጎበኙ ሲሆን በተለይም በቨርቲካል አግርካልቸር የተሰራውን ስራ ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙርያ፣ በናኖቴክኖሎጂ የምርምር ውጤቶች፤ በአፍላክቶክሲን፤ ከስኳር ተረፈ ምርቶች ላይና ከወዳደቁ ፕላስቲኮች የተሰራውን የቤት ፓርተሽኖችና የወለል ንጣፎችን እና ከባጋስ የተሰራውን ብርከት ከሰል፤ ሀይል ቆጣቢ የእንጀራ ምጣድ፤ የፎውል ኮለራ የዶሮ በሽታ ክትባት እንድሁም በላበራቶሪ የተደገፉ በርካታ የምርምር ስራዎችን ከተመለከቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ባዩት ነገር መደሰታቸውንና ወደፊት ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ 
በጉብኝታቸው ወቅት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሴት ሳይንትስቶች በምርምር ስራው ላይ የተመለከቱ መሆናቸው ያስደሰታቸው መሆኑን በመጦቆም ጠንካራ አመራር ባለበት ቦታ ሁሉ ውጤታማ ስራዎች ስከናወኑ ይሰተወላሉ በማለት አስተያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባዮቴክሎጂ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ካሳሁን ተስፋዬ እና ም/ዋና ዳይሬክተሮች በዋናነት ቋሚ ኮሚቴውን በማስጎብኘት ስመሩ የነበሩ ሲሆን ስለ ተቋሙ አጠቃላይ ገለጻ ለቋሚ ኮሚቴው አብራሪቷል፡፡ 
የቋሚ ኮሚቴው አባለት የኢንስቲትዩቱን ተመራማሪዎች ያለባቸውን የላብራቶር መሰረት ልማት እጥረቶች፤ በቂ የሆነ የኢንሲቲትዩቱ ህንጻ አለመኖሩ፤ የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ውስንነቶች ከቀረበላቸው ሪፖርት የተገነዘቡ ሲሆን አግባብነት ያለውን እገዛ ሁሉ ለማድረግ ቃል የገቡ መሆናቸውን አክለው በመግለጽ አሁን ያለው ትውልድ ግን መስዋትነት ከፍለው የተሻለ ሃገር ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት በኃላፍነት ስመት ስራዎች መከናወን እንዳለብት ግልጸዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እምዬ ቢተው ተቋሙ ከተቋቋመ ገና ሶስት አመት ያልሞላው ቢሆንም አሁን እያከናወነ ያለውን በጎ ጅምሮች እያጠናከሩ መሄድና ምርምሮችን ወደ ውጤት በመቀየር ህዝባችንን ተጠቃሚ ማደረግ የሚሉት ወደፊት ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡