Asset Publisher Asset Publisher

Back

የባዮቴክኖሎጅ ማህበር ምስረታ የመስራቾች የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ማህበር ምስረታ የመስራቾች የምክክር መድረክ ጥር 21/2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንቲትዩት ውስጥ ተካሄደ፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ካሳሁን ተስፋዬ በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመልዕከታቸውም የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንቲትዩትና የማህበሩ መቋቋም በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ ያላቸውን አስተዋፅዖ በመግለጽ ማህበሩ መቋቋም በሀገራችን ስለሚካሄዱ የባቴክኖሎጂ የምርምር ስራዎች ከመደገፍና ሀገራዊ መልክ እንዲኖረው በማድረግ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በዚህ ዙርያ በመገንባት የህብረተሰቡን ድምጽ በመሆን ከመስራት አኳያ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው በመግለጽ ወደ ምስረታ መምጣት መቻሉ የሚያኮራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከ ከኢትዮጵ ግብርና ምርምር የባየቴክኖሎጂ፡ ዳይሬክተር በመድረኩ ላይ የተገኙት ዶ/ር ታደሰ ዳባ የማህበሩን ምስረታ አስመለክቶ የማህበሩን ሚና በተመለከተ የተናገሩ ሲሆን በንግግራቸውም ይህ ማህበር የባለሙያዎች ማህበር እንደ ሆነና በባዮቴክኖሎጂ ዙርያ ያሉትን የተለያዩ ፍልዶችንና ባለሙያዎችን  ወደ አንድ የሚያሰባስብ፤ መሰራት የሚገቡ የምርምር ስራዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የሚለይ፤ ጆርናሎች ማሳተም፤ ትልልቅ ፈንድ የማፈላለግና አዋርድ ማድግ፤ አለም አቀፍ ሰሚናሮችን የማዘጋጀትና የማስተባበር ሚና የሚኖረው እነደሆነ ያብራሩ ሲሆን ማህበሩ ራሱን የቻለና ከየትኛውም ነገር ነጻ በመሆን የሚቋቋም ነሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡

አቶ ዬሐንስ ስጦታ እና አቶ አዳነ ገበየሁበምክክር መድረኩ ላይ ማህበር ስለ ማቋቋምና በጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ ውስጥ ስላለው አስፈላጊ መስፈርቶች፤ የማህበሩ ስያሜና የማህበሩን መተደደርያ ደንብ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የማህበሩ ገቢ ምንጭ በተመለከተም የማህበሩ ገቢ ምንጭ ከማህበሩ አባለት፤ ከህዝባዊ ድጋፍ፤ ከእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች፤ ገቢ ከሚያስገኙ በማፈላለግ እንደሚሆን ባለሙያዎቹ በመግለጽ የማህበሩ መደበኛ አባል ለመሆንም በባዮተክኖሎጂ እና በባዮቴክኖሎጂ ዘርፎች/sub specialty / ላይ የትምህርት ዝግጁነት ያለው ማነኛውም ባለሙያ የመተዳደርያ ደንንቡን መስፈርት የሚያሟሉ ከሆነ አባል መሆን የሚቻል መሆኑን ተናግሯል፡፡

በመጨረሻም የተቅላላ ጉባዔ መድረክ በቀጣይ ሰኔ ወር ውስጥ የሚካሄድ መሆኑን ከምክክር መድረኩ መስማት ተችሏል፡፡