የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ጀመረ!!!
ኢንስቲትዩቱ በባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂዎች ምንነትና አስፈላጊነት ዙሪያ መጋቢት 18 እና 19 /2010 ዓ.ም በወንድራድ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ እና በስኩል ኦፍ ቱሞሮ ት/ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫው የተሰጠው በዘርፉ ተመራማሪዎች በዋናነት የተቋሙ የምርመር የትኩረት ዘርፎች በሆኑት በጤና ባዮቴክኖሎጂ፣ ግብርና ባዮቴክኖሎጂ፣ በአካባቢ ባዮቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪያል ባዮቴክኖሎጂ ፣ በናኖቴክኖሎጂ፣ በምልሰ ምህንድስና፣ በማቴሪያል ሳይንስ እና አርቲፊሽያል ኢንተለጀስ ቴክኖሎጂዎች ዙርያ ላይ በርካታ ምሳሌዎችን አጋዥ በማድርግ ሲሆን ተማሪዎቹም ላነስዎቸው አንዳንድ ጥያቄዎች በቂ ማብራሪያን ተደርጎላቸዋል፡፡
አላማውም ከግንዛቤ መፍጠር ባሻገር ቴክኖሎጂዎቹ ለሃገር ያላቸውን ፋይዳ አጉልቶ በማሳየት ተተኪ የዘርፉ ሙህራን በማፍራት የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ማስቀጠል ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ እና በቀጣይም በሌሎች ማህበራትና ት/ቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጫው እንደሚቀጥል ተገልጻል፡፡
Call for proposals 2018 Biotechnology click here for more
Artificial Intelligence directorate of Ethiopian Biotechnology Institute has organized a workshop on Artificial Intelligence for Ethiopia in collaboration with Hawassa University. The workshop includes paper presentation and panel discussion on applications of AI in health, agriculture, education and automation sectors.Therefore we would like to invite you to participate on this workshop as presenter or panelist. Please fill out the following form so that we can review your work.