Asset Publisher Asset Publisher

Back

ምልስ ምህንድስና ለኢትዮጵያ ግብርና

ምልስ ምህንድስና ለኢትዮጵያ ግብርና

ሀገራት ቀጣይነት ላለው የምጣኔ ሃብት ዕድገትና የህዝባቸውን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ትኩረታቸውን ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ለውጥ በማምጣት ላይ አድርገዋል:፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ከሌሎች ታዳጊ ሀገራት የተለየች አይደለችም፡፡ ኢትዮጵያ እንደሚታወቀው ለቴክኖሎጂ አዲስ አይደለችም፤ በተለይም በስነ-ህንጻ፣ በስነ-ጽሁፍ እና በህክምና እጅግ የበዛ ሀብት ባለቤት ናት፡፡ ያላትን ሀብት በተደራጀ መልኩ ባለማስተላለፍና በተለያዩ የውጪ ወራሪዎች በመዘረፍ ሀብቷን በአግባቡ ሳትጠቀም ቀርታለች፤ ሌሎች ሀገራት ከሁዋላ ተነስተው አሁን ከፊት ሆነዋል፡፡ በአሁኑ  ስአት ኢትዮጵያ ከምንም በላይ የሚያስፈልጋት አዳዲሰ ዘዴዎችን በመቀየስ እንደ በፊቱ ሳይሆን፤ አሻጋሪ የሆነ የቴክኖሎጂ ዉጤት ወይም ዘዴ ያስፈልጋታል፡፡ በተለይ የግብርና ዘርፉ በጣም ሁዋላ ቀር ከመሆኑ የተነሳ ህዝባችንን መመገብ እንኳዋ አልቻለም፡፡ ከሺ ዘመን ጀምሮ ስንጠቀምበት የነበረውን በበሬ በአድካሚ ሁኔታ ማረስ አልቀየርነውም፤ አሁንም ከዕርዳታ አላመለጥንም፡፡ የሚሊኒየም ግቡን በተለይም እራስን በምግብ መቻልን ለማሳካት የተለያየ የተሸሻሉ የግብርና መሳሪያዎችንና ዘዴዎችን መጠቀም ይኖርብናል፡፡ ለዚህም ትልቅ ምሳሌ የሚሆኑት ሀገራት እንደ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን የመሳሰሉት ሀገራት፣ በልሎች ሀገራት የተስሩና በጣም የተሻሻሉ የቴክኖሎጂ መሳሪዎችን በሀገራቸው አስመስለው በመስራት ወይም ደግሞ ለሀገራቸው እዲመች አድርገው በመቅዳት፣ ለምርምርና አዳዲስ ላልተሞከሩ የቴክኖሎጂ ስራዎች  የሚያወጡትን ጊዜና የሰው ሀብት እንዲሁም ገንዘብ ሊቀንሱ ችለዋል፡፡ ይህም አስመስሎ የመስራት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በፍጥነት ለማምጣት የሚያስችል የምህንድስና ዘርፍ ምልስ- ምህንድስና (reverse engineerig) ይባላል፡፡ ሀገራችን ይህን የቴክኖሎጂ ዘዴ በመጠቀም በተለይም የተሻሻሉ የግብርና መሳሪያዎችን መልሶ በመስራትና ከአገልገሎት ውጪ ለሆኑ ትራክተሮች መለዋወጫ በማምረት፤ የግብርናውን ዘርፍ በምልስ ምህንድስና እድገቱን ማፋጠን ይቻላል፡፡

ምልስምህንድስና(ReverseEngineering) ዑደትሲሆንሰውሰራሽዕቃንበመበታተንናዉስጣዊአሰራሩንበማጥናት፣የተሰራበትንጥሬዕቃበመለየት፣ዲዛይኑንበማጤንበአጠቃላይወይምበተወሰነመልኩየዕቃዉንየአመራረትዑደትበመረዳትመልሶመስራትማለትነዉ፡፡ይህምዑደትየሚጀምረዉከሃሳብ(ከዲዛይን)ሳይሆንከዕቃዉሞዴልበመነሳትዲዛይንይዘጋጅናምርቱይመረታል፡፡በአጠቃላይበሌሎችአገሮችየሚሰሩቴክኖሎጂዎችንወደሚፈለግበትአገርአደፕትለማድረግናለዚያአገርበሚጠቅምዓውድለመስራትየሚንጠቀምበትአሰራርነው፡፡ ይህምበተለያዩአገሮችለተለያዩጥቅምሲዉልእነመለከታለን፡፡

በጃፓን፣በእርሻሥራላይአድካሚየሆኑአሰራሮችንለመቀነስበምልስምህንድስናበሰሩኣቸዉቴክኖሎጂዎችእየተጠቀሙይገኛሉ፡፡ሰፋፊየሆኑማሳዎቻቸዉንዉሃማጠጣት፣የመድኃኒትርጭትየሚያከናዉኑትምበዚሁቴክኖሎጂበሰሩአቸዉድሮኖችነዉ፡፡ኢራኖችደግሞበስለላላይየነበረችዉንየኣሜሪካንንድሮንበመጥለፍናየምልስምህንድስናቴክኖሎጂበመጠቀምየራሳቸውየሆነዉንድሮንበመስራትበዓለምላይተፅእኖእየፈጠሩይገኘሉ፡፡እነዚህምድሮኖችለተለያዩአገልግሎቶችለምሳሌበመከላከያ፣ለእርሻስራ፣ሰዉሰራሽወይምየተፈጥሮአደጋበሚደርስበትወቅትለመቆጣጠርናለሌሎችምአገልግሎቶችይጠቀሙባቸዋል፡፡ ደ/ኮሪያውያንበአገራቸውያለዉንየጥናትናምርምርሥራዎችንበማጠናከርናየምልስምህንድስናቴክኖሎጂዎችንበብዛትበኤሌክትሮንክስናበአዉቶሞቢል(ከአሜሪካ)እዲሁምደግሞበኬሚካል፣ሲሚንቶእናየመዲኃኒትአመራረትቴክኖሎጂዎችን(ከቱርክ)በመዉሰድ(አዶፕት)በማድረግበዓለምላይተወዳዳሪለመሆንበቅታለች፡፡በአጠቃላይምልስምህንድስናጊዜናገንዘብከመቆጠብምባለፈዘርፈብዙጥቅሞችአሉት፡፡ በአሁኑወቅትበኢትዮጵያባዮቴክኖሎጂኢንስቲትዩት(ኢ.ባ.ቴ.ኢ)ስርባለዉበምልስምህንድስናእየተሰሩካሉስራዎችመካከልአፈርአልባየሽቅብእርሻእናየእርምጃትራክተርቴክኖሎጂዎችይገኛሉ፡፡አፈርአልባየሽቅብታእርሻ(ሃይድሮፖኒክቴክኖሎጂ)በከፍተኛሁኔታበማደግላይየሚገኘውየህዝብቁጥር፣የከተሞችመስፋፋት፣የውሃአቅርቦትእጥረትእንዲሁምየአየርንብረትለውጥየእርሻመሬትእንዲቀንስየራሳቸውንአስተዋጽዖአድርገዋል፡፡ይህምየእርሻመሬትመቀነስበፍጥነትእያደገያለውንየህዝብቁጥርለመመገብአዳጋችያደርገዋል፡፡ይህንችግርለመፍታትናአስተማማኝየምግብአቅርቦትለማሟላትየሽቅብእርሻትልቁንድርሻይጫወታል፡፡ስለሆነምኢትዮጵያለሽቅብታእርሻቴክኖሎጂትኩረትሰጥታበግብርና፣በምግብዋስትናበከተማግብርናፖሊሲዎችንበማዘጋጀትማካተትአለባት፡፡ይህንበተመለከተየሚያጋጥሙችግሮችንፖሊሲበመቅረጽመከላከልእናመቆጣጠርይቻላል፡፡የከተማግብርናየምግብናየገቢምንጭከመሆንበዘለለለከተማውህብረተሰብአካባቢያዊጠቀሜታምስላለዉየከተማግብርናእቅድንተግባርላይማዋልአስፈላጊነው፡፡ምንአይነትእፅዋትእናየግብርናዘዴእንደሚጠቀሙምቁጥጥርማድረግአስፈላጊነዉ፡፡ሽቅብግብርና(ሃይድሮፖኒክቴክኖሎጂ)አፈርአልባቴክኖሎጂሲሆንበከተማዉስጥብዙቦታበማይፈጅመልኩየተለያዩየአትክልትናፍራፍሬማምረትየሚያስችልቴክኖሎጂነው፡፡ስለሆነምአፈርአልባ(ሃይድሮፖኒክቴክኖሎጂ)መጠቀምየከተማዉንህብረተሰብተጠቃሚማድረግይቻላል፡፡ይህምቴክኖሎጂበጥቂቱከሚያካትታቸዉፋሲሊትዎችጥላ(ግሪንሃዉስ)፣መደርደሪያ፣ፒቪሲ፣የዉሃመስመሮችናቸዉ፡፡ነገርግንእንደፒቪሲ፣ስቲልብረቶችንየማናገኝከሆነአከባቢያችንበቀላሉከሚናገኛቸዉዕቃዎች(እንጨት፣ቀርከሃ፣፣የዉሃማጠጫቱቦዎች)በመጠቀምማዘጋጀትይቻላል፡፡በሃይድሮፖኒክቴክኖሎጂያለአፈርፈሳሽማዳበሪያበመጠቀምየተለያዩአትክልቶችንለምሳሌሰላጣ፣ቆስጣ፣ቲማቲምእናሌሎችአትክልቶችንማምረትይቻላል፡፡  

የእርምጃትራክር(WalkingTractor)በኢትዮጵያዉስጥየእርምጃትራክተርቴክኖሎጂአዲስአይደለም፡፡ ነገርግንከዋጋውውድነትናየተነሳበስፋትለመጠቀምአልተቻለም፡፡ሙሉለሙሉበኢትዮጵያውስጥለማምረትየጥሬዕቃናየማምረትአቅምውስንነትስለነበረበታሰበዉልክወደዳዛይንናምርትለመግባትአልተቻለምነበር፡፡በአሁንጊዜካለውከመንግስትምሆነከባለድርሻአካላትተነሳሽነትየተነሳከግብርናመርወደኢንዱስትሪመርእድገትመሸጋገርስላለብንእናይህንንምለማፋጠንእደነእነዚህዓይነትቴክኖሎጂዎችንመልሶበመስራትየኢንዱስትሪውንናየግብርናውንዘርፍማስተሳሰርናማጠናከርአስፈላጊከመሆኑምራስንበምግብለመቻልየተያዘውንእቅድለማሳካትከፍተኛአስተዋፆያደርጋል፡፡

በግብርናውዘርፍያለውየቴክኖሎጂአጠቃቀምውስንነትየተነሳበአጠቃላይበአገሪቱላይያለውንየግብርናምርትናየምግብውጤቶችላይአሉታዊተጽእኖእየፈጠረይገኛል፡፡ለዚህምእንደችግርበዋናነትየሚጠቀሰውየአመራረትስርዓታችንለብዙዘመናትበበሬከማረስልንላቀቅአለመቻለችንነው፡፡ይህንንችግርለመፍታትየተለያዩቴክኖሎጂዋችንበምልስምህንድስናበመታገዝበአገራችንዓውድመሰርትበማላመድቴክኖሎጂውንማስረጽአማረጭየሌለውመፍትሄነው፡፡በዚህምመሰረትበምልስምህንድስናባለሙያዎችናኢንጂነሮችእየተሰራያለውየእርምጃትራክተርቴክኖሎጂተስፋየሚጣልበትነው፡፡ይህምቴክኖሎጂበአገራችንውስጥባለጥሬዕቃበመጠቀምናየተወሰነውንየትራክተሩንኣካልበምልስምህንድስናቴክኖሎጂበማጠናት፣

ደዛይንበማድረግናበማምረትላገራችንገበሬጠቀሜታእንዲውልለማስቻልስራዎችአየተሰሩነው፡፡ይንንስራእዉንለማድረግየተለያዩየቅድመዝግጅትጥናትእንዲሁምየሙከራዲዛይንስራዎችበኢ.ባ.ቴ.ኢእየተሰሩይገኛሉ፡፡በዲዛይንስራውወቅትከሚካተቱነገሮችውስጥየኢትዮጵያየመሬትአቀማመጥ፣የአየርሁኔታናየአፈርዓይነትበዋናነትከግምትዉስጥበማስገባትእናለዚህተመጣጣኝየሆነአቅምያለውየእርምጃትራክተርሰርቶማሳያለማምረትበስራደትላይነው፡፡በዚህሁኔታበሙሉኣቅምማምረትከተቻለተመጣጣኝበሆነዋጋምርቱንበማቅረብበአገሪቱላይእየታየያለውንየማምረትአቅምበማሳደግየግብናዘርፉንአንድእርምጃለማሳደግያግዛል፡፡ምልስምህድስናእንደኢትዮጵያላሉታዳጊሃገራትናራሳቸውንበምግብለመቻልለሚጥሩ፤ እዲሁምግብርናቸውንዘመናዊበማድረግተጠቃሚለመሆንእንዲችሉየሚያግዝዘርፍነወ፡፡ 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


አሥር ምርጥ የ2017 ዓም ኢመርጂንግ ቴክኖሎዎጂች አሥር ምርጥ የ2017 ዓም ኢመርጂንግ ቴክኖሎዎጂች