Asset Publisher Asset Publisher

Return to Full Page

በኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ፓሊሲ ረቂቅ ላይ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሄደ

የሁለት፡ ቀናት፡የምክክር፡መድረክ፡በባዮቴክኖጂ፡ረቂቅ፡ፓሊሲ፡ዙሪያ፡ በኢትዮጵያ፡ ባዮቴክኖሎጂ፡ ኢኒስቲትዩት፡ ተደረገ፡፡

መስከረም19/2010፡የፓሊሲው፡ ረቂቅ፡ጽሁፍ፡ቀርቦ፤ሰፋ፡፡ያለና፡ በተሳታፊዎች ፡ባለቤትነት፡ስሜት፡ በተሞላበት፡መልኩ፡ወይይት፡ተደርጔል፡፡

ተሳታዎች/ባለድርሻ አካላት/ ፡- ከሳይንስና፡ቴክኖጂ፡ሚኒስቴር፤ከትምህርት፡ሚኒስቴር፤ከአዲስ፡አበባ፡ዩኒቨርሲቲ፤ከብሄራዊ፡የእንስሳት፡ጤና፡ጥበቃ፡ኢኒስቲትዩት፤ከሀዋሳ፡ዩኒቨርሲቲ፤ከአዲስ፡አበባ፡ሳይንስና፡ቴክኖሎጂ፡ዩኒቨርሲቲ፤ከመቀሌ፡ዩኒቨርሲቲ፤ከጅማ፡ዩኒቨርሲቲ፤ከአዳማ፡ሳይንስናቴክኖሎጂ፡ዩኒቨርስቲ፤ከባህርዳር፡ዩኒቨርሲቲ፤ከጎንደር፡ዩኒቨርሲቲ፤ከደብረብርሀን፡ዩኒቨርሲቲ፤ከወልቂጤ፡ዩኒቨርሲቲ፤ከሀረማያ፡ዩኒቨርሲቲ፤ከኢትዮጵያ፡ግብርና፡ምርምር፡ኢኒስቲትዩት፤ከሆለታ፡ግብርና፡ምርምር፡ኢኒስቲትዩት፤ከኢትዮጵያ፡ብዝሀ፡ህይወት፡ኢኒስቲትዩት፤ከኢትዮጵያ፡የሕብረተሰብ፡ጤና፡ኢኒስቲትዩት፤ከኢትዮጵያ፡ሳይንስ፡አካዳሚ፤ከብሄራዊ፡የእንስሳት፡ጤና፡ምርመራና፡ምረምር፡ማዕከል፤ከኢትዮጵያ፡የአካባቢና፡ደን፡ምርምር፡ ኢኒስቲትዩት፡ከፓሊሲና፡ምርምር፡ማዕከል፡ከእርሻናተፈጥሮ፡ሀብት፡ሚኒስቴር፤ከኢንዱስትሪ፡ሚኒስቴር፡ከጤና፡ጥበቃ፡ሚኒስቴር፤ከዋጊኖስ፡ባዮቴክ፤ከእንስሰት፡ሀብት፡ሚኒስቴር፤ከትምህርት፡ሚኒሰቴር፤ከኦሮሚያ፡ግብርና፡ምርምር፡ኢኒስቲትዩት፤ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ፡ባዮቴክኖሎጂ፡ፓሊሲ፡ረቂቅ፡የባለድርሻ፡አካላት፡ውይይት፡አስፈላጊነት(አላማው)

  • ባለድርሻ፡አካላት፡ሁሉ፡የኢትዮጵያ፡ባዮቴክኖጂ፡ፓሊሲ፡ባለቤት፡እዲሆኑ፡
  • በፓለሲው፡ውስጥ፡ያሉ፡ጉዳዮች፡ግልጽ፡የተብራሩ፡እንዲሆኑ፡
  • ገንቢ፡የሆኑ፡ተጨማሪ፡ሀሳቦች፡እንዲገኙ፡
  • ፓሊሲው፡ሙሉ፡ሆኖ፡ እንዲዘጋጅና፡እዲጸድቅ፡፡

በእለቱ፡የተደረጉ፡ንግግሮች ፡-

በመጀመሪያ፡የእንኳን፡ደህና፡ መጣችሁ፡ንግግር፡ያደረጉት፡ ዶ/ር፡ ካሳሁን፡ተስፋዮ፡ የኢትዮጵያ፡ባዮቴክኖሎጂ፡ኢኒስቲትዩት፡ዋና፡ዳሬክተር ናቸው፡፡

እንዲሁም፡ከሳይንስ፡ቴክኖሎጂ፡ሚኒስቴር፡ሚኒስትር፡ዴኤታ፡ኘ/ር፡አፈወርቅ፡ካሱ፡የመርሃ፡ግብር፡መክፈቻ፡ንግግር፡ተደርጔል፡፡በተጨማርም፡ስለ፡ባዮቴክኖሎጂ፡ኢኒስቲትዩት፡አጠቃላይ፡ገጽታ፡ሀላፊነት፡በዶ/ር፡አለምነህ፡ጌቶ፡ቀርቧል፡፡በመቀጠልም፡የኢትዮጵያ፡ፓሊሲ፡ረቂቅ፡ሰነድ፡በኢትዮጵያ፡ባዮቴክሎኖጂ፡ኢኒስቲትዩት፡ም/ዋና፡ዳይሬክተር፡ዶ/ር፡ሀይሉ፡ዳዲ፡ቀርቧል፡፡የኢትዮጵያ፡ባዮቴክኖጂ፡ፓሊሲ፡ረቂቅ፡ላይ፡ተሳታፊዎች፡በአራት፡ጉዳዮች፡በቡድን፡ተከፍለው፡እነዚህም፡አቅም፡ግንባታ(ቡድን1)፤ምርምር፡ስርአት(ቡድን2)፤ማስተባበርናቅንጂት(ቡድን3)፤የህግ፡ማቀፍ፡(ቡድን4)በመመደብ፡ከፍተኛ፡ሀላፊነትና፡የሙያ፡ብቃት፡የታየበት፡ጠንካራ፡ውይይት፡ተደርጎ፡ጠቃሚ፡ግኝቶች፡ቀርበዋል፡፡በአራቱ፡ጉዳዮች፡የተከፈለው፡የተሳታፊ፡ቡድን፡ውይይት፡የተሰባሰቡ፡ግኝቶች፡በዝርዝር፡ቀርበዋል፡ለረቂቅ፡ፓሊሲው፡ግብዓት፡ሆነዋል፡፡

በሁለተኛው፡ቀን፡ መስከረም 20/2010፡ደግሞ፡የኢትዮጵያ፡ባዮቴክኖጂ፡የሰው፡ሀብት፡ልማት፡ፕሮጀክት፡እና፡ የኢትዮጵያ፡ባዮቴክኖጂ መሰረተ-ልማት፡ፕሮጀክት፡ሰነዶች፡ቀርበው፡ሰፋ፡ያለ፡ውይይት፡ተካሂዶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም፡ማጠቃለያ፡እና፡የወደፊት፡አቅጣጫ፡በሚመለከት፡ንግግር፡ያደረጉት፡ዶ/ር፡ካሳሁን፡ተስፋዬ፡የኢትዮጵያ፡ባዮቴክኖሎጂ፡ኢኒስቲትዩት፡ዋና፡ዳይሬክተር፤ኢኒስቲትዩቱ፡በህግ፡የተሰጠውን፡መብት፡በዘርፉ፡ያሉ፡ክፍተቶችን፡በመለየት፡ተገቢውን፡ምላሽ፡እንዲያገኙ፡ኢኒስቲትዩቱ፡እደሚጥር፡ገልጸዋል፤ለሚመለከተው፡አካል፡እንደሚያቀርብና፡ምላሽ፡ለማግኘት፡ጥረት፡እንሚያደርግ፡ገልጸዋል፡፡ከላይ፡ ውይይት፡ ለተደረገቸባው፡ርዕሰ፡ጉዳዮች፡ላይ፡ለሚሰሩ፡ስራዎች፡ከተሳታፊዎች፡መካከል፡ሰባት፡አባለት፡ያሉበት፡ኮሚቴ፡ለእያንዳዳቸው፡አስመርጠዋል፡፡

የኢኒቲትዩቱ፡ማስተባበር፡ድጋፍ፡ሰጪ፡ሀላፊነቱን፡እንደሚወጣ፡በማስታወስ፡የባለድረሻ፡አካላት፡ቀጥተኛ፡ተሳትፎ፡እንሚያስፈልግ፡

አስገንዝበዋል፡፡