Asset Publisher Asset Publisher

Return to Full Page
Back

ፕሮፊሰር ሶስና ሀይሌ በኢ.ባ.ቴ.ኢ ጉብኝት አደረጉ

ታህሳስ 26 2010 ዓ.ም  በአለም በኢነርጂ እና በ ማትሪያል ሳይንስ  እውቋ ፕሮፊሰር ሶስና ሀይሌ  ኢ.ባ.ቴ. ኢ. ተገኝተው ጉብኝት ነበር፡፡ በኢኒሲትዩቱ  ዋና ዳይሬከተር  በወሳኝ የኢኒስትዩቱ ዳይሬክቶሪየቶች ላይ ሰፋ ያለ ገለጻ ተደረጎላቸዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ከ ገለጻቸው በኋላ ኢኒሲተዩቱ ትብብሮች እና ሙያዊ ግነኙነቶች ፤ አጭርና ረጅም ስልጠናዎች ፤እንዲሁም የላብራቶሪ መሳሪያዎች ስለጠና እንደሚያስፈልግ ገልጸውላቸዋል፡፡ እሳቸውም በጣም የተደሰቱና ይህንን ለማድረግ ፍቃደኛ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጻዋል፡፡ በመቀጠልም  ባዮና ኢመረጂንግ ማዕከላትና የኮርፓሬት አስተዳደር ጸ/ቤት እንደዚሁም ግንባታቸው በማለቅ ላይ ያሉትን የባዮና የኢመርጂንግ ቤተ- ሙከራዎች ጎብኝተዋል፡፡ በመጨርሻም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሄደው  የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴሩንና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴሩን ድኤታውን ያአገኙ ሲሆን በውይታቸውም አብሮ ለመስራት የሚያስችል ፕሮፖዛል በኢነረጂ ዙረያ ተቀረፆ መስራት እንደሚፈልጉ መግባባት ላይ ድርሰዋል፡፡ ወጣት ባለሙያዎች ወደ ውጭ በመውሰድ ለማሰልጠን እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ ፕሮፊሰር ሶስና ሀይሌ  ‘MIT’ ከተባለ ተቋም ዲግሪያቸውና ዶክትሬታቸውን አግኝተዋል ፡፡እንደዚሁም ማስተርሳቸውን ካሊፎሪኒያ ዩኒቨሲቲ አግኝተዋል፡፡ የድኅረ ዶክትሬት ደግሞ ‘Stuttgrat’  በጀርመን አገር ሰርተዋል፡፡በተለያዩ በአሜሪካ በሚገኙ የቴክነኖሎጂ ኢነስቲትዩቶች ሰርተዋል፡፡የተለያዩ ሽልማቶችም አግኝተዋል፡፡አሁን  እየሰሩት ያሉት ስራ  ‘’ከውሀ ካርበን ዳይኢክሳይድን በመለየት’ የሶላር ነዳጅ ‘ እንዲፈጠር ‘በቴርሞኬሚካል’ ሂደት አዲስ መንገድ የፈጠረ የጸሀይ ብርሀን በመጠቀም የሐይል ፍላጎትን ማርካት ‘’የሚያስችል ስራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡