Back

ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችን የመፍጠር ጅማሮ

በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የትምህርት ተደራሽነት ቢጨምርም ጥራት ላይ ግን አሁንም ችግሮች እንዳሉ በተለያዩ መድረኮች ይገልፃል፡፡ በተለይም ትምህርት አሰጣጡ ተግባር ተኮር ያለመሆኑ ብቁ የሰው ኃይልን ለማፍራት ማነቆ እንደሆነም ይነሳል፡፡ በዚህም አገሪቱ በየዓመቱ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሰለጠኑ ዜጎችን ብታፈራም፣ የምታከናውናቸውን ፕሮጀክቶች ግን ከባህር ማዶ በመጡ ባለሙያዎች ሲሰሩ ይታያል፡፡
ይህም በአንድ በኩል በትምህርት ሂደቱ በሌላ በኩል ደግሞ ከውጭ ዕውቀትን ማስገባቷ ለኪሳራ እየዳረጋት እንደሆነም አይካድም፡፡ ይህንን ችግርም ለማቃለል በየጊዜው የተለያዩ ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡ በቅርቡም የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
መልክ ከቁመናው በአስተሳሰቡም እንከን እማይገኝለት ሆኖ እንዲወለድና «ወይ መልክ አይ ስብዕና የተሟላ ውበት ማለት ይሄ ነው» የሚያሰኝ ልጅ ከሆድ እያለ መፍጠር ዓለም የደረሰበትን የሥልጣኔ ጥግ ያሳያል፡፡ የመድኃኒት ውጤታማነትን የሚያሳድግና ከሕፃናት አታርቁ የሚለውን መመሪያ የሻረ ዘረመል ተወስዶ የሚቀመም ፈዋሽ መድኃኒትም በቴክኖሎጂ ምጥቀት የተሳካ መሆንን የሚጠይቅ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ግን ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች እንዳሉ በጊብሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲ.ኤም.ሲ ቅርንጫፍ የ11ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ክፍል ተማሪ ሀና ተስፋዬ ትናገራለች፡፡
ተማሪ ሀና፣ በቀን ሦስት ጊዜ እንኳን መብላት ለማይችሉት በሳይንሳዊ መንገድ የበለፀገ ምግብን እንዲዘጋጅ ማድረግ የሚቻልበት መንገድ አገር ውስጥ ቢሰራበት የምግብ ዋስትናን ያግዛልም ባይ ናት፡፡ በቀጣይ ዘመናዊ አስተራረስን የሚያጎለብቱና በተለይም በአሁኑ ወቅት የግብርናው ችግር የሆነውን ተምች ለማጥፋት የሚረዳ ቴክኖሎጂ እንዲፈልቅ ለመስራት ዕቅድ እንዳላትም ጠቁማናለች፡፡ ይህን መሰል ሥልጠና ለአገሪቱ ዕድገት ወሳኝ በመሆኑም ሁሉንም ተማሪዎች ባካተተ መልኩ ቢሰራ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብም ይቻላል፡፡ በተጨማሪም 10ኛ ክፍል ላይ ቢሰጥ ተማሪዎች በየትኛው የትምህርት መስክ መሰማራት እንዳለባቸው እንዲወስኑ ያደርጋቸዋል በማለት ከታች ጀምሮ መስጠትና መሰራት እንደሚኖርበት ትገልፃለች፡፡

source: http://www.ethpress.gov.et/addiszemen/index.php/society/item/17426-2018-04-30-19-42-20


Web Content Display Web Content Display

 The growth in the profile of drones has surely by now moved out of the folder marked ‘fad’. Where once flying model aircraft was seen as a fairly niche hobby, enjoyed by men with sensible jackets and thick-rimmed glasses, now seemingly everyone wants to get in on the drone act.

Read More.....

Web Content Display Web Content Display

AI will lead to humans losing their jobs and widespread redundancy – that’s the theory, anyway. However new research has suggested that firms which are investing in smart, automated and self-teaching systems are more likely to be creating jobs with it.

Read More......

Web Content Display Web Content Display

We hope to contribute to the thriving field of AI ethics and social impact through original interdisciplinary research that also draws upon technical insights from our team, expertise from other disciplines, and the voices of people affected by the development of these new technologies. Our research themes reflect the key ethical challenges that we believe exist for us and the wider AI community. We intend to undertake research and collaborations in each of these areas, with our priorities determined  by the differing degrees of urgency of the challenges ahead.

Read More......