Asset Publisher Asset Publisher

Return to Full Page

የናኖ ቴክኖሎጂ ጥቅሞች

ናኖ ቴክኖሎጂን የሚያጠኑ ተመራማሪዎች፣ ቴክኖሎጂው ድህነትን ከመቅረፍ ባሻገር፣ ሞትን እስከማስቀረት የሚደርሱ ጠቀሜታዎች እንደሚያስገኝ ገልጻሉ፡፡ ቴክኖሎጂው ተቀባይነት ሲያገኝና በስፋት ተግባር ላይ ሲውል፣ የሰዎችን ሕይወትና አኗኗር ሙሉ ለሙሉ የመለወጥ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ናኖ ቴክኖሎጂ (ናኖ) በአንፃራዊነት ዕይታ ሲቃኝ አዲስ የምርምር ዘርፍ እንደሆነ ይገለጻል፡፡ በመሆኑም የዘርፉ ተመራማሪዎችም ሆኑ ሌሎች ባለሙያዎችን የሚያስማማ ትርጓሜ ሊገኝለት አልቻለም፡፡ የዘርፉ ተመራማሪዎች ናኖ ቴክኖሎጂ በአጠቃላይ ከአንድ እስከ መቶ ናኖ ሜትር መጠን ባለው ደረጃ የሚደረጉ ምርምሮችን ለመግለጽ የሚውል መጠሪያ ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን ከመጠናቸው ይልቅ በተጠቀሱት አኃዞች ደረጃ የሚገኙ ቁሶች የሚያሳዩዋቸው ባህርያት እጅግ ጠቃሚ ናቸው የሚሉም አሉ፡፡

ስለጉዳዩ መጽሐፍ የጻፉትና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂው የሕግ ተመራማሪ ኃይለ ሚካኤል ተሾመ (ዶ/ር)፣ ቁሶች በዚህ መጠን የሚያሳዩዋቸው ባህርያት አስደናቂ እንደሆኑ ያስረዳሉ፡፡ ለምሳሌ በተፈጥሮው ቢጫ ቀለም ያለው ወርቅ በናኖ መጠን የአተሞቹን (‹‹አተም›› ወይም  ‹‹አቶም››  ሁሉም ቁስ የተገነባበትረታዊ እኑስ ነው። እንደ ግዝፈታቸው መጠናቸው የተያየ ስም ያላቸው ልዩ ልዩ ዓይነት አተሞች አሉ። እነዚህ የተለያዩ ዓይነት አተሞች የኬሚካልንጥር ይባላሉ)፣ ቦታ በመለዋወጥ የተለያዩ ቀለማትንና የጥንካሬ ደረጃን እንዲያመጣ ማድረግ ይቻላል ይላሉ፡፡

‹‹ቫዝሊን ለስላሳና ስንነካውም ምንም የመቆርቆር ስሜት አያሳይም፡፡ ነገር ግን በናኖ መጠን ላይ ምርምር ሲደረግ መንኮራኩር ወደ ጠፈር ተሸክሞ ሊያወጣ የሚችል አሳንሰር ለመሥራት የሚያስችል ጥንካሬ ያሳያል፡፡ ይህም በውስጡ ያሉትን አተሞችና ሞለኪዩሎች ቦታ በመቀያየር የሚሠራ ነው፤›› በማለት አብራርተዋል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ