Web Content Display Web Content Display

ሰለ ኢንስቲትዩቱ

የኢትዮዽያ ፌደራላዊ ደሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 አንቀፅ 5 አና 39 መሰረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ደንብ አውቷ የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 388/2008 ተቋቋመ፡፡ ኢንስቲትዩቱ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሆኖ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሚመራ የተለያዩ ሚኒስተር መስራያ ቤቶች ሚንስተሮች፣ የኢንስቲቱቱን ዋና ዳይሪክተርና ሌሎችን ያሳተፈ የባዮቴክኖሎጂ ካውንስል ተቋቁሞ የሚመራ ተቋም ነው፡፡

የኢንስቲትዩቱ መቋቋም አስፈላጊነት በዩኒቨርስቲ እና በምርምር ተቋማት ተበታትኖ ያሉ ስራዎችን ለመደገፍ፣ የምርምር ስራዎችን የሚመራ  ተቋም በማስፈለጉ፣ ለህብረተሰቡ ቀዳሚ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ፣ ጤና እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ፣ የሀገሪቱ የቀጣይ ኢኮኖሚ ዋልታ ይሆናል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን የኢንዱስትሪ ዘርፍ በጥሩ መሰረት ላይ ለመጣል ፣ በቂ አቅም እና የአሰራር ስርዓት የሚዘረጋ እና በበላይነት የሚቆጣጠር እንዲሆን  የሚሉት ከብዙው በጥቂቱ  ናቸው፡፡

ኢንስቲትዩቱ በዋናነት ለሀገር ልማት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ባላቸው የባዮና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂዎች ውጤቶች ላይ የምርምር ሥራዎችን በማካሄድና ተመሳሳይ ምርምሮችን በመደገፍ የሰው ሃብት ልማት ለሚያፋጥኑ ተመራማሪዎች ምቹ ሁኔታን ፈጥሮ የምርምር አቅም በፍጥነት በመገንባት፣ የማህበረሰቡን እሴትና ሞራል በማይቃረኑ መልኩ ደረጃውን የጠበቀ ምርምር እንዲኖር በማስቻል  ለሕብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ጠቀሜታ እንዲውል ማድርግ ዋና አላማው ነው፡፡፡

ኢንስቲትዩቱ በ1ዋና ዳይሬክተርና በ2 ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እና ተጠሪነታቸው ለኮርፖሬት ዳይሪክተር ጽ/ቤት የሆነ አራት ዳይሬክቶሬቶችን እና ተጠሪነታቸው ለዋና ዳይሪክተር የሆነ ስድስት ዳይሪክቶሬቶችን የያዘ ኢንስቲትዩታዊ መዋቅር ያለው ነው፡፡ ተቋሙ አሁን የሚጠራበትን ስያሜ ያገኘው  የኢትዮጵያ ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከሚሉ ሁለት ስያሜዎች በሃላ ነው ፡፡ ነገር ግን ስያሜው ባዮቴክኖሎጂ ይሁንእንጂ የኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ስራዎችንም በጋራ በማደርግ  የላይፍ ሳይንስ እና ፊዚካል ሳይንስን  አጣምሮ  እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡

ሁለቱን በጋራ ማደራጀት ያስፈለገበት ምክንያት ቴክኖሎጂዎቹ ብዙ ዘርፎችን አቀናጅተው በትስስር ለማስኬድ ማስቻላቸው ፣ በውስን የሙያ ዘርፍ ድንበር ሳይወሰኑ ቅንጅታዊ የምርምር አቅምን መጠቀም ማስቻሉ ፣የኢንደስትሪ ባዮቴክኖሎጂ በራሱ ኤንዛይም፣ ኬሚካሎችንና የመሳሰሉትን ማምረት አንዲችል የናኖቴክኖሎጂ እና ማቴሪያል ሳይንስ መሰረታዊ እውቀት ማስፈለጉ ፣ በቆዳ፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በባዮ-ኢነርጂ በምግብና መጠጥ ኢንደስትሪው ላይ ለውጥ ኢንዲመጣ ያንዱ እውቀን ላንዱ በማስፈለጉና ሁለንተናዊ የእርስበእርስ ትስስርና ተያያዥነት ያለቸው እና ተደጋጋፊ የቴክኖሎጂ ዘርፎች በመሆናቸው የእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ስብጥር ማስፈለጉ ታሳቢ ተደርጎ የተደራጀ ኢንሲቲትዩት ነው፡፡

ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ሠዓት 18 የዶክትሬት ዲግሪ፣ 44 የማስተርስ፣ 40 የመጀመሪያ ዲግሪና 5 ዲፕሎማ ያላቸው በአጠቃላይ 104 ሠራተኞች ቀጥሮ በማሰራት ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ ሰራተኞቹ በዋናነት

በባዮቴክኖሎጂ ስር በሚገኙ

 • በጤና ባዮቴክኖሎጂ፣

 • በግብርና ባዮቴክኖሎጂ፣

 • በአካባቢ ባዮቴክኖሎጂ፣

 • በኢንዱስትሪያል ባዮቴክኖሎጂ እና

 • በባዮኢንፎርማቲክስና ጀኖሚክስ፡፡

በኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ስር በሚገኙ

 • በናኖቴክኖሎጂ፣

 • በምልሰ ምህንድስና፣  

 • በማቴሪያል ሳይንስ እና

 • አርቲፊሽያል ኢንተለጀስ በሚባሉ ተቋሙ ትኩረት በሰጣቸው ዘጠኝ የትኩረት መስኮች ላይ መሰረት ጥለው ሃገራችን ኢትዮጵያ ከግብራና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱሰትሬ መር ኢኮኖሜ የሚታደርገውን ፈጣን ሽግግር በሳይንሱ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤትን በማምጣት እና በመደገፍ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡

ግንቦት 2009

 

Vision Vision

Vision

To see product and services of biotechnology and emerging technologies utilize by our citizens as effective tools and innovative solution in their daily life.

 

Mission Mission

Mission

To provide world class research, innovation and community service in order to improve citizens' quality of life and to significantly contribute for the national economic development via the synergetic endeavor of biotechnology and emerging technologies 

 

Values Values

Values

 • Integrity
 • collaboration
 • Continuous Learning
 • Critical Thinking 
 • Making Difference